Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም እንዳላት ተመልክተናል – ፒርስ ኦክላጋን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮችን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም እንዳላት ተመልክተናል አሉ የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን፡፡

ፒርስ ኦክላጋን በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘውን የአደይ አበባ ዓለም አቀፍ የመለማመጃ ትራክና በመገባደድ ላይ የሚገኘውን ስታዲየም በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የጀግኖች አትሌቶች መፍለቂያ ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጨምሮ የተለያዩ ውድድሮችን የማዘጋጀት ሙሉ አቅም እንዳላት ተመልክተናልም ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ የተሰሩ የአትሌቲክስ መሰረተ ልማቶችን ያደነቁት ፒርስ ኦክላጋን ÷ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ወደ ከፍታ ለማምጣት ሁለንተናዊ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

በቀጣይ ዘመኑን የዋጀ ብቁ የአትሌቲክስ የሰው ሃይል ማደራጀትና የስፖርት ቴክኖሎጂ ማጎልበት ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አበክሮ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version