አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ክልክል ነው አለ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ።
በዚህም መሰረት ከነገ የካቲት 4 ማለዳ ጀምሮ እስከ ማክሰኞ የካቲት 10/2018 ዓ.ም ድረስ በከተማዋ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከልክሏል፡፡
ክልከላው የፀጥታና በመንገድ ትራፊክ አገልግሎት ዘርፍ የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን፥ የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይህንን ጊዜያዊ ክልከላ በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ ርምጃ እንደሚወሰድ ቢሮው አሳስቧል፡፡
የአፍሪካ ኅብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ነገ እና ከነገ በስቲያ እንዲሁም የኅብረቱ መሪዎች ጉባኤ የካቲት 7 እና 8 በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

