Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

19 ሺህ 600 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 19 ሺህ 600 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ።

የክልሉ ሻይ፣ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት 21 ሺህ ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ 19 ሺህ 600 ቶን ምርት ማቅረብ ተችሏል።

በክልሉ ኮረሪማ፣ ዕርድ እና ዝንጅብል በስፋት እንደሚመረቱ ጠቅሰው÷ አሁን ላይ የቁንዶ በርበሬ ምርት በልዩ ትኩረት በመልማት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል ብለዋል።

ወደ ግብይት የሚገቡት የቅመማ ቅመም ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ በመሆናቸው የማልማት አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱንም አመልክተዋል።

በሲሳይ ለገሰ

Exit mobile version