Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለሶማሊያ እና ሱዳን ዘላቂ ሰላም የጋራ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሊያ የተገኘው ሰላምና መረጋጋት እንዳይቀለበስና ለሱዳን ዘላቂ ሰላም የጋራ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፡፡

ከ48ኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ አባል የሆነችበት የኅብረቱ የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዷል፡፡

በስብሰባው ላይ በአኅጉሪቱ ወቅታዊ ሰላምና ጸጥታ ሁኔታ በተለይም ሶማሊያና ሱዳን ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ በቀጣናው ሰላምና ጸጥታን ለማስፈን ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገራት ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈላቸውን አስታውሰዋል።

አሸባሪው አልሸባብ በሶማሊያ ሰላምና ጸጥታን የማወክ እንቅስቃሴውን ቀጥሏል ያሉት ሚኒስትሩ፥ በሀገራቱ መስዋዕትነት የተገኘው ሰላምና መረጋጋት እንዳይቀለበስ በሽብር ቡድኑ ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሚኒስትሩ በንግግራቸው በሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉንም ሱዳናውያን ያካተተ የመፍትሔ ጥረት መደረግ አለበት ነው ያሉት፡፡

Exit mobile version