Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባዔ የአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ማዕቀፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባዔ የአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ማዕቀፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ ነው አለ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፤ ከአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ አስቀድሞ የአፍሪካ ጣሊያን ጉባዔ እንደሚካሄድ ጠቅሰዋል።

ይህም የአፍሪካ-ጣሊያን ግንኙነት በአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የትብብር ማዕቀፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ጣሊያን ጉባዔ በአፍሪካ ሲደረግ የመጀመሪያ ሲሆን÷ መዳረሻው ኢትዮጵያ መሆኑ ሀገሪቱ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ከማስተሳሰር አንፃር ያላትን ከፍተኛ አቅም የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የጉባዔው ማዕከላዊ አጀንዳ በፈረንጆቹ 2024 በሮም ይፋ የተደረገውን የማቴይ ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ እንደሆነ አብራርተዋል።

የጉባዔው ዋና ዋና አምዶች በሆኑት ኢነርጂ፣ ግብርና፣ ትምህርትና ስልጠና፣ ጤና፣ ውሃ እና መሰረተ ልማት ኢትዮጵያ በርካታ ተሞክሮዎችን ማቅረብና አጋርነቶችን ለመመስረት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚትገኝ አመልክተዋል።

በአድማሱ አራጋው

Exit mobile version