አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኬንያ የካቢኔ፣ የውጭና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ ሚኒስትሮች ከ48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት፥ የሀገራቱን የሁለትዮሽና ቀጣናዊ የትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
