አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ብሔራዊ ጥቅሞቿን የሚያስጠብቁ አጀንዳዎች አቅርባለች።
የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ሁለተኛ ቀን ውሎው በሰላምና ፀጥታ ላይ መክሯል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የሕብረቱን የሁለተኛ ቀን ውሎና የኢትዮጵያ ተሳትፎን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም ሕብረቱ በአፍሪካ ሰላምና ደኅነንት፣ በሶማሊያና ሱዳን እየታዩ ያሉ የፀጥታ ስጋቶችን መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከሩን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያም እንደ ቀደመው ሁሉ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ሚናዋን እንደምትወጣ አረጋግጣለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ የራሷን አጀንዳ ከማንፀባረቅ ባሻገር ለአሕጉሪቱ አጀንዳ 2063 መሳካት የበኩሏን ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ አብራርተዋል።
ከሕብረቱ የስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከፈረንሳይና ኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር መክረዋል ብለዋል።
በውይይቱ የሀገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ፍሬያማ ውይይት ተደርጓልም ነው ያሉት።
አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞዋ ለሌሎች ተሞክሮ በመሆን ጭምር ስብሰባውን በማስተናገድ ላይ እንደምትገኝም አብራርተዋል።
በሰለሞን በየነ

