አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባዔ ከክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቀረበለትን ከ743 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጽድቋል።
የክልሉ ምክር ቤት ያጸደቀው በጀት መደበኛ እና የካፒታል ፕሮጀክቶችን ለማስፈፀም እንደሚውል መመላከቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
በተጨማሪም የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባዔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቅቋል።

