አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አቢሲኒያ ባንክ ባዘጋጀው የሽልማት መርሐ ግብር ለዕድለኛው ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ አፓርታማ አስረክቧል።
ባንኩ የዲጂታል መተግበሪያን በመጠቀም የሚደረጉ ግብይቶችን ለማበረታታትና አዳዲስ የዲጂታል ባንክ ደንበኞችን ለማፍራት ባዘጋጀው መርሃግብር ዕጣ ለወጣላቸው ደንበኞቹ ሽልማታቸውን አስረክቧል።
የባንኩ ዲጂታል ባንኪንግ ዋና ኦፊሰር ሶስና መንገሻ ለዕድለኛው የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ ባስረከቡበት ወቅት እንዳሉት፥ ባንኩ ደንበኞች ባሉበት ሆነው ሁሉንም የባንክ አገልግሎቶች የሚያገኙበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አቅርቧል።
መርሐ ግብሩ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከ10 ሚሊየን በላይ ግብይቶች መከናወናቸውንና ከ138 ቢሊየን ብር በላይ መንቀሳቀስ መቻሉንም ተናግረዋል።

