Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቡሩንዲ የ2026 የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነትን ከአንጎላ ተረከበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ የ2026 የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፥ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በዚሁ ወቅት ቡሩንዲ የ2026 የኅብረቱን ሊቀመንበርነት በይፋ የተረከበች ሲሆን፥ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤቫሪስት ንድዪሺሚዬ ከአንጎላ አቻቸው ዣዎ ሎሬንሶ ጋር ርክክብ በበማድረግ ሥራቸውን ጀምረዋል።
Exit mobile version