Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሲዲ ኡሉድ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሲዲ ኡሉድ (ዶ/ር) ጋር በቡድን 20 ስብሰባ ወቅት ከነበረን ውይይት የቀጠለ ምክክር አድርገናል ብለዋል።
ውይይቱም በአካታች እድገት ድጋፍ፣ በልማት ፋይናንስ እና በመላው አፍሪካ ስለሚኖር ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት የተመለከተ መሆኑን ገልጸዋል።
Exit mobile version