አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) ጋር መወያየት ሁልጊዜም አስደሳች ነው ብለዋል፡፡
በውይይታቸውም በዘላቂ ልማት፣ በኢኮኖሚ እድገት እና ለአፍሪካ ልማት የቅድሚያ ጉዳዮችን በተመለከተ መምከራቸውን ተናግረዋል፡፡
ውይይቱ ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ውይይት የቀጠለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡

