አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት መፍትሄ ጥምረት ፕሬዚዳንት ጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያ በተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሁኔታና የፖሊሲ ለውጦች ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡
ጄፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዙ ምክረ ሃሳቦችን አጋርተዋል፡፡

