አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቺልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (ሲአይኤፍኤፍ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያይተዋል።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ ከሲአይኤፍኤፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬቲ ሃምፕተን እና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን ጎብኝተናል ብለዋል።
በጉብኝታቸውም በቀጣይ በጋራ በምንሠራባቸው የትኩረት መስኮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ነው ያሉት።

