አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሦስት አዳዲስ የሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማሪፊያዎች በሚያዚያ ወር ተመርቀው ስራ ይጀምራሉ አለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ።
አየር መንገዱ ባወጣው መረጃ÷ በግንባታ ላይ ከሚገኙት የሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማሪፊያዎች መካከል በመጪው ሚያዚያ ወር ሦስቱን በማስመረቅ በረራ ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።
እነዚህ አዳዲስ መዳረሻዎች ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ መቱ እና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውንም አመልክቷል።

