Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

89ኛው የየካቲት12 ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያውያን የአልገዛም ባይነት ጽናት የታየበት 89ኛው የየካቲት12 ሰማዕታት ቀን መታሰቢያ በዓል በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት ፊት ለፊት ተከብሯል፡፡

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ አባትና እናት አርበኞች በመገኘት የአበባ ጉንጉን በማኖር የሰማዕታቱን መስዋዕትነት ዘክረዋል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን በዚህ ወቅት÷ ወጣቱ ትውልድ አያትና ቅድመ አያቶቹ ለሀገር ፍቅርና አንድነት የከፈሉትን የሕይወት መስዋዕትነት በማሰብ ሀገሩን ከጠላት ጥቃት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

በጌታሰው የሺዋስ

Exit mobile version