Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አስተማማኝ የሳይበር ደኅንነት ስርዓት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ስኬታማ ለማድረግ አስተማማኝ የሳይበር ደኅንነት ስርዓት መገንባት ወሳኝ ነው አሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ።

የመንግሥት አገልግሎቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የቆዩ አሰራሮችን በማስቀረት ለኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እና ለቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ መሰረት መጣል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አገልግሎቶቹ ወደ ዲጂታል ሲቀየሩና የተጠቃሚ ቁጥር ሲያድግ የሳይበር ጥቃቶችም በዚያው ልክ ውስብስብ እየሆኑ እንደሚመጡ ጠቅሰዋል።

ኢመደአ ይህንን ስጋት ለመመከትና የሀገሪቱን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚያስችሉ ጥብቅ ስታንዳርዶችንና የህግ ማዕቀፎችን እያዘጋጀ መሆኑን አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ ይህንን የገለጹት ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ስትራቴጂካዊ የሳይበር ደኅንነት ንቃተ-ህሊና ስልጠና ባስጀመሩበት ወቅት መሆኑን የተቋሙ መረጃ አመልክቷል።

Exit mobile version