አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ከዎልቭስ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ ተለያይቷል።
የሊጉ መሪ አርሰናል በቡካዮ ሳካ እና ሂንካፒ ግቦች 2 ለ ዐ ሲመራ ቢቆይም፥ በሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ ለሚገኘው ዎልቭስ ቡዪኖ እና ካላፊዮሪ (በራሱ ላይ) ባስቆጠሯቸው ግቦች ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ 27 ጨዋታዎችን ያደረገው አርሰናል በ58 ነጥብ ሊጉን ሲመራ፥ 26 ጨዋታዎችን ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ በ5 ነጥብ ልዩነት ይከተላል።

