አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዋሽ ኢንሹራንስ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሆን ዲጂታል የጉዞ ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎትን አስጀምሯል።
የጉዞ ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎቱ ተደራሽ፣ ተስማሚ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ መሆኑ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡
አገልግሎቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሞባይል መተግበሪያ የሚሰጥ መሆኑንም አዋሽ ኢንሹራንስ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በሁለቱ ተቋማት አጋርነት የቀረበው የጉዞ ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት የተቋማቱን የደንበኞች አገልግሎት ማሳለጥ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

