Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ቦርዱ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል የሚያስችል ብሔራዊ የትብብር ስምምነት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሐሰተኛና አደናጋሪ ምርጫ ነክ መረጃዎችን ለመከላከል የሚያስችል ብሔራዊ የትብብር ስምምነት ይፋ አድርጓል፡፡

ብሔራዊ የትብብር ስምምነቱ ይፋ በሆነበት ወቅት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ÷ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግልፅ፣ ተዓማኒ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ሀሰተኛ መረጃዎች በምርጫ ወቅት ተፅዕኖ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ጠቅሰው÷ ብሔራዊ የትብብር ስምምነቱ ይህንን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ነው ያሉት፡፡

የብሔራዊ ትብብር ስምምነቱ ዓላማ በምርጫ ሂደት ሊሰራጩ የሚችሉ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለማጣራት እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ስምምነቱ መራጮች እና በምርጫው ድርሻ ያላቸውን ተቋማትና ግለሰቦች በተዛባ መረጃ ላይ ከተመሰረተ ውሣኔ አሰጣጥ እንዲጠበቁ ለማድረግ እንዲሁም ምርጫው ነፃ እና ተዓማኒ መሆኑን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

Exit mobile version