Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተዳፍኖ የቆየውን የዓድዋ ድል ዳግም በኩራት እንዲያንሠራራ አስችሏል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ተዳፍኖ የቆየው የዓድዋ ድል ዳግም በኩራት እንዲያንሠራራ አስችሎታል አሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነች የዘንድሮው የዓድዋ ድል ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ጠዋት በዓድዋ ድል መታሰቢያ በታላቅ ድምቀት መከበሩን ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ በዚህ ወቅት እንኳን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ተዳፍኖ የቆየው የዓድዋ ድል ዳግም በኩራት እንዲያንሠራራ ማስቻሉን አውስተዋል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ትናንት በደማቸውና በአጥንታቸው የሀገርን ዳር ድንበር ያስከበሩ ሕዝባቸውንም በክብር ያኖሩ ጀግኖች መታሰቢያ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በዚህ ስፍራ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን የዓድዋን 130ኛ ዓመት እንደ ስሟ አበባ በሆነችው አዲስ አበባ በታላቅ የማስ ስፓርት አክብረነዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
Exit mobile version