አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ሊቨርፑል ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸንፏል።
አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሊቨርፑል 1 ለ 0 ነው ያሸነፈው።
የጨዋታው ሙሉ ጊዜ ተጠናቅቆ በተጨመረ የባከነ ደቂቃ ላይ አሌክሲስ ማካልስተር የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ወልቭስን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ኢቫን ጉሳንድ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ አሳርፏል።
እንዲሁም ፉልሃምን ከሰንደርላንድ ባገናኘው ጨዋታ ፉልሃም 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ራውል ሂሚኔዝ በጨዋታና በፍጹም ቅጣት ምት እና አሌክስ ኢዎቢ የፉልሃምን ግቦች ሲያስቆጥሩ ኢንዞ ለፊ ደግሞ የሰንደርላንድን ብቸኛ ግብ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።
የሊጉ ጨዋታ ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1:30 ላይ ቶተንሀምን ከአርሰናል የሚያገናኘው የሰሜን ደርቢ ጨዋታ ይጠበቃል።

