Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እናሰራለን በሚል ከ6 ሚሊየን ብር በላይ በመቀበል የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳዳር መሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ ሰራተኞች ነን፤አመራሮችን እናውቃለን፤ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እናሰራላችኋለን በማለት 6 ሚሊየን 362 ሺህ 59 ብር አታልለው በመቀበል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ቶማስ ማናዬ ተበጀ፣ ሳሙኤል ኪዳኔ ሃይሌ፣ ፅዮን አበራ ጣፋ፣ ዳዊት መንግስቱ እና ሚኪያስ አውላቸው ናቸው፡፡

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በ2017 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳዳር ክልል ውስጥ የግል ተበዳይ አቶ መሬት ስፋ 3 ሺህ 825 ካ.ሜ ላይ የከብት ማድለቢያ አገልግሎት ለማዋል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመሰራት ሒደት ላይ ያለ መሆኑን ያውቃሉ፡፡

ይህን በመረዳትም እኛ የመሬት ልማትና አስተዳዳር ቢሮ አመራር ሹፌር እና ጸሐፊ ነን፤ አብረናቸው ነው የምንሰራው ካርታ በአስቸኳይ እናሰራልሃለን በማለት ከላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ይቀበላሉ፡፡

ገንዘቡን ከተቀበሉ በኋላም ከአከባቢው በመሰወራቸው በቀረበ ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ክትትል ተይዘው በ12/06/2018 ዓ.ም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version