አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 130ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ሐሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ÷ ዳግማዊ ዓድዋን የሚገልጹ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ላይ መገኘታችን 130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
በዓሉ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር የገለጹት ሚኒስትሯ÷ ዓድዋ ከኢትዮጵያውያን ባሻገር የመላው ጥቁር ሕዝቦች ድል በመሆኑ ይህንን የሚገልጹ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ተናግረዋል።
በበዓሉ ተሞክሮዎችን ማጋራት የሚያስችሉ እና የሰራዊቱን ጉዞ የሚያሳዩ የተለያዩ ዝግጅቶች በዐውደ ርዕይ እንደሚቀርቡ አንስተው÷ በክብረ በዓሉ የተለያዩ ሀገራት የጦር መሪዎችና ሚኒስትሮች እንደሚታደሙ አመልክተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ

