Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየተገበረች ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየተገበረች ነው አለ የግብርና ሚኒስቴር፡፡

የዓለም  የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ያዘጋጀው ግብርና እና የደን ልማትን በማቀናጀት ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ የሚኒስትር ዴዔታ አማካሪ ምትኩ አያሌው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየተገበረች ነው፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ጨምሮ የአፈር ለምነትን የሚያረጋግጡ ትግበራዎችን በመቅረፅ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ገልጸው ሂደቱ ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

የፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ ኦርላንዶ ሶሳ በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ በደን ልማት እና ደንን ያማከለ የእርሻ ትግበራ እውን ለማድረግ እያከናወነች ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

መድረኩ የመስክ ምልከታን ጨምሮ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ደን ሳይጨፈጨፍ የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው የመፍትሔ ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በወንድሙ አዱኛ

Exit mobile version