Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

172 ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ክትባት ዕቅድ ላይ እየተሳተፉ ነው – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት 172 ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተዘጋጀው እቅድ ላይ እየተወያዩ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሃገራት በትብብር እና በቅንጅት መስራት ይገባቸዋልም ብለዋል፡፡

አያይዘውም በቅድሚያ ውስን የክትባት አቅርቦት የሚኖር ከሆነ ክትባቱን በቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ አካላት ማድረስ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የእቅዱ አካል መሆን የሚፈልጉ ሃገራት እስከ ፈረንጆቹ ነሃሴ ወር መጨረሻ ድረስ ፍላጎታቸውን በማሳወቅ መስከረም ላይ ምላሽ እንደሚያገኙ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ምክክር እየተደረገበት ያለው ዓለም አቀፉ የኮቪድ19 ክትባት በዓለም ጤና ድርጅት፣ በቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ በተቋቋመው ጋቪ የክትባት ህብረት እና ሴፒ ተብሎ በሚጠራው የተላላፊ በሽታዎች ዝግጁነት ህብረት አማካኝነት የሚመራ ነው ተብሏል፡፡

እቅዱ አልቆ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነም የኮሮና ክትባትን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሃገራት ማዳረስን አላማው ያደረገ ነው፡፡

ምንጭ፣ ሬውተርስ

Exit mobile version