Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያውያን ለብሔራዊ ጥቅማቸው በጋራ መቆም የዘመናት መገለጫቸው ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን ለብሔራዊ ጥቅማቸው በጋራ መቆም የዘመናት መገለጫቸው ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፡፡

ቢሮው 130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በማስመልከት “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ዓድዋ የኢትዮጵያውያን የማድረግ አቅም የተገለጠበት ታላቅ ድል ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን በየትኛውም ጊዜ በሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም በጋራ መቆም መገለጫቸው ነው ያሉት ኃላፊዋ÷ አሁንም እንደ ሀገር ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ በሚሰሩ ሥራዎች ዓድዋን መሠረት ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ባንዳዎች እንደሚፈትኗት አንስተው÷ ተግባራቸው ግን በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድና ሀገር ወዳድነት ይመከታል ነው ያሉት፡፡

በሰለሞን ይታየው

Exit mobile version