Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ቡና ነጌሌ አርሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ነጌሌ አርሲን 1 ለ 0 አሸንፏል።

አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናን ማሸነፊያ ግብ ራምኬል ጄምስ (ፍ) ከመረብ አሳርፏል።

በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተደረገው የመቻል እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ተጠናቅቋል።

ቀደም ሲል በተደረገው የሊጉ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ አዳማ ከተማ እና ሸገር ከተማ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡

Exit mobile version