Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በፍርድ ቤቶች የተዘረጋው የዲጂታል ስርዓት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፍርድ ቤቶች የተዘረጋው የዲጂታል ስርዓት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል አለ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የተዘረጋው የዲጂታል ስርዓት ባለ ጉዳዮች የፍርድ ሒደቱን ባሉበት ሆነው እንዲከታተሉ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡

በአሁን ወቅት በፌደራልና በክልሎች እየተዘረጋ የሚገኘው የዲጂታል ስርዓት ባለጉዳዮች ከቀጠሮ ጀምሮ እስከ ፍርድ ያለውን ጉዳይ ባሉበት ሆነው እንዲከታተሉ እድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

በተለያዩ ፍርድ ቤቶች የዲጂታል ስርዓት ትግበራ ተደራሽ ባልሆኑ ቦታዎች በማስፋት ተግባራዊነቱ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዲጂታል ስርዓት አካል የሆነው የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር አሰራርን በቅርቡ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በቀጣይ የጨረታ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የዲጂታል ስርዓቱ ቀደም ሲል ባለጉዳዮች በይግባኝ ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ይመላለሱ የነበረበትን ሁኔታ በመቀየር አሁን ላይ የዲጂታል ስርዓቱን ባሉበት  ሆነው እንዲከታተሉ እድል መፍጠሩን አብራርተዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

Exit mobile version