Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሊቨርፑል ዌስትሃም ዩናይትድን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ዌስትሃም ዩናይትድን 5 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ለሊቨርፑል ሁጎ ኤኪቲኬ፣ ቨርጂል ቫን ዳይክ፣ ማክ አሌስተር፣ ኮዲ ጋክፖ እና አሌክስ ዲሳሲ (በራስ ላይ) ግቦቹን ሲያስቆጥሩ፤ ለዌስትሃም ቶማስ ሶቼክ እና ቫሌንቲን ካሲያኖ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።

በሌላ በሌላ ጨዋታ ኤቨርተን ወደ ኒውካስትል ዩናይትድ አቅንቶ 3 ለ 2 ሲያሸንፍ፤ በተመሳሳይ ከሜዳው ውጪ የተጫወተው ብሬንትፎርድ በርንሌይን 4 ለ 3 አሸንፏል፡፡

አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ቦርንማውዝ እና ሰንደርላንድ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

Exit mobile version