Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ሴቶች በማናቸውም ሕገ መንግስቱ ባረጋገጣቸው መብቶችና ጥበቃዎች ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡

በዚሁ መሠረት የመንግስት ሕጋዊ ማዕቀፎች የሴቶችን ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ማሳደግ በሚያስችል መልክ ይቀረጻሉ፡፡

ለምሳሌ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች እጩ ሲያቀርቡ ተገቢው የሴቶች ውክልና እንዲኖራቸው የሕግ ግፊትና ማበረታቻም ከመንግስት ይደረጋል፡፡

በዚህ ረገድ ፓርቲዎች ባቀረቡት የሴቶች እጩ ብዛት ላይ የተመሰረተ የምርጫ ወጪ መሸፈኛ ድጎማ ከመንግስት የሚያገኙበት አሰራር ተዘርግቷል፡፡

የፖሊቲካ ፓርቲዎች በየደረጃው ያሉትን አመራሮቻቸውን ሲመርጡም የጾታ ውክልና እንዲኖራቸው የህግ ግፊትና ማበረታቻ ለማድረግ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ ቁ. 1162/2011 ውስጥ ተካቷል፡፡

Exit mobile version