Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምርጫ፣ የሥነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት…

በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 124 መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች በቂ ምርጫ ነክ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ስልት በመቀየስና የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት ይሰጣል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ቦርዱ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት መስጠት እንዲችሉ ህጋዊ ሰውነት ላላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የትምህርት ተቋማት፤ የማስተማር ፈቃድ ይሰጣል፡፡

አንድ መራጮችን ለማስተማር የሚፈልግ ድርጅት ፈቃድ እንዲሰጠው ለቦርዱ ሲያመለክት በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 125 መሠረት መስፈርቶች ማሟላት አለበት፡፡

መስፈርቶቹም፡-
1. በህግ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ወይም እውቅና ያለው የከፍተኛ ትምርህት ተቋም መሆኑን፤
2. ለመራጮች ትምህርት ያወጣውን መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን፤
3. ተግባሩን ለመወጣት የሚያስችል ብቃት ያለው መሆኑን፤
4. ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ገለልተኛ መሆኑን፤

እነዚህ መስፈርቶች ሲሟሉ ቦርዱ ያዘጋጀውን የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ ሥነ ምግባር መመሪያ መቀበላቸውን ድርጅቱንና ወኪሎቹን በማስፈረም የማስተማር ፈቃድና መታወቂያ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡

Exit mobile version