Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሂጅራ ባንክ የመጀመሪያውን የዘካ ገንዘብ ለዘካና አውቃፍ ኮሚሽን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሂጅራ ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ታሪክ የመጀመሪያውን የዘካ ገንዘብ ለዘካና አውቃፍ ኮሚሽን አስረክቧል።

ባንኩ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ለተቋቋመው የዘካ እና አውቃፍ ኮሚሽን የዘካ ገንዘብ የማስረከብ ስነስርዓት በዛሬው ዕለት አከናውኗል፡፡

ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው ባንኩ 8 ሚሊየን 182 ሺህ ብር የዘካ ክፍያ አስረክቧል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ፣ የዘካና አውቃፍ ኮሚሽን የቦርድ አመራሮች፣ የባንኩ የሸሪዓ አማካሪዎች፣ የዑለማዕ ምክር ቤት ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ባንኩ ያስረከበው ገንዘብ ባለፈው 2017 ካስመዘገበው ዓመታዊ ትርፍ የተገኘ ሲሆን፥ ከርክክብ ስነስርዓቱ ጎን ለጎን የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂዷል።

የዘካና አውቃፍ ኮሚሽን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባለፈው ሰኔ ወር መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version