አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቴምር ፕሮፐርቲስ የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ዜጎች የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ከ200 በላይ አቅመ ደካማ የማሕረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ 800 ሰዎች መሳተፋቸው ተመላክቷል።
በተጨማሪም በዚህ ወቅት ተቋሙ ለካሊድ ፋውንዴሽን የ5 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በሪል እስቴት ዘርፍ ተሰማርቶ የሚገኘው ቴምር ፕሮፐርቲስ በአዲስ አበባ የመኖሪያ እና የንግድ ህንጻዎችን በመገንባት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከመመለስ ጎን ለጎን የተለያዩ ማሕበራዊ ኃላፊነቶችን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
በሚልኪያስ አዱኛ

