Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አምስት ጨዋታዎች ሲደረጉ አርሰናል ከብራይተን ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ሊጉን በ64 ነጥብ እየመሩ የሚገኙት መድፈኞቹ በሜዳቸው ኢምሬትስ በተደረገው የመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ብራይተንን 2 ለ 1 በሆነ ጠባብ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

በብራይተን አሜክስ ስታዲየም ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ላይ በሚካሄደው ጨዋታም አርሰናል ከብራይተን ብርቱ ፉክክር ሊገጥመው እንደሚችል ተገምቷል፡፡

በአርሰናል በኩል ቼልሲን ድል ባደረጉበት ጨዋታ በጉዳት ተቀይሮ የወጣው ዴክላን ራይስ ለጨዋታው የመድረሱ ጉዳይ አጠራጣሪ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት አርሰናልን በአምስት ነጥብ ልዩነት እየተከተለ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኤቲሃድ ስታዲየም ኖቲንግሃም ፎረስትን ያስተናግዳል፡፡

በሳምንቱ የእረፍት ቀናት ሽንፈትን ያስተናገዱት አስቶንቪላ እና ቼልሲ በቪላ ፓርክ ጨዋታቸውን በተመሳሳይ 4 ሰዓት ከ30 ላይ ያደርጋሉ፡፡

ፉልሃም ከዌስትሃም ዩናይትድ በተመሳሳይ ሰዓት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን÷ ኒውካስል ዩናይትድ ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ይደረጋል፡፡

Exit mobile version