Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 960 ኪ.ግ አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 960 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገለጸ።
 
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ ተማረ÷ ትናንት ጠዋት በአይሱዙ የጭነት ተሸከርካሪ አደንዛዥ እፅ ጭኖ ከአዲስ አበባ ወደ ባሕርዳር አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ሊያዝ መቻሉን ተናግረዋል።
 
ተጠርጣሪው ተሸከርካሪውን አቁሞ ለጊዜው ከአካባቢው መሰወሩን የገለጹት ኃላፊው በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
 
ዋና ኢንስፔክተር ደሳለኝ የአደንዛዥ እጹ ምንነት ለጊዜው በውል ባለመታወቁ በምርመራ ለመለየት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
 
ሃላፊው አያይዘውም ከአደንዘዥ እጹ ጋር 43 ኩንታል የእንስሳት መኖ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አብሮ በመጫን ለሽፋን መጠቀማቸውን ገልጸዋል።
 
በቀጣይም ህብረተሰቡ እንዲህ አይነት አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት ለፖሊስ በማሳወቅ ወንጀልን በመከላከሉ ሂደት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪያቸውን ማስተላለፋቸውን አብመድ ዘግቧል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
 
Exit mobile version