Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሙስሊሞች ጋር የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሙስሊሞች ጋር የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂደዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዛሬ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን ጋር የአብሮነት መገለጫ በሆነችው በውቧ አራዳ ፓርክ የኢፍጣር መርሐ ግብር አካሂደናል ብለዋል።

ወቅቱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የረመዳን ጾም፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች በታላቁ ዐቢይ ጾም ወደ ፈጣሪ ይበልጥ የሚቀርቡበት መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ከወትሮው በተለየ ያለ ሃይማኖት ልዩነት እርስ በርስ የምንጠያየቅበት፣ የምንደጋገፍበት፣ የምንተሳሰብበትና ‘ምን ጎደለ?’ የምንባባልበት ልዩ ጊዜ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ወገኖች ጋር የሚደረገው የኢፍጣር መርሐ ግብር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተው፤ የከተማዋ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ተምሳሌት የማድግ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

Exit mobile version