1. የመራጭነት ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ይሰጠዋል፤
2. እያንዳንዱ የመራጭነት ምዝገባ መታወቂያ ካርድ መራጮች በመራጮች በመዝገብ ላይ ከተመዘገቡ በኋላ ከመዝገቡ ጋር እየተገናዘቡ የሚሞሉ የሚከተሉት አምዶች ይኖሩታል፤
ሀ) የመራጭ ስም ከነአያት፣
ለ) የሚኖርበት ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ ምርጫ ጣቢያ፣ የቤት ቁጥር፣ መንደር ወይም ጎጥ፤
ሐ) የመዝገብ ቁጥር፣ የመዝገብ ተራ ቁጥር፣ የመራጭ መለያ ቁጥር እና የመዝገብ ገጽ፤
መ) የመራጭ ዕድሜ፤
ሠ) የመራጭ የምልክት ወይም የአውራ ጣት ፊርማ፣ የመዝጋቢ ፊርማ እና
ረ) የተመዘገቡበት ቀን፤
3. አንድ መራጭ አንድ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ብቻ ይኖረዋል፡፡
4. ለምርጫ የተመዘገበ ሰው በድምፅ መስጫው ዕለት የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ ይዞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ አለባት፡፡
5. የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ የጠፋ መሆኑ በማስረጃ ሲረጋገጥ ወይም የተበላሸበት መራጭ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ባለበት ጊዜ፣ የመራጮች መዝገብ ለሕዝብ ግልጽ በሚደረግበት ጊዜ ወይም በምርጫው ቀን በማንኛውም የምርጫ ጣቢያው የሥራ ጊዜ የምርጫ ጣቢያው ምትክ ካርድ እንዲሰጥ ማመልከት ይቻላል።
6. መመዝገቡ ከምርጫ ጣቢያው መዝገብ ከተረጋገጠ በኋላ በቃለ ጉባዔ ተይዞ በምትኩ ሌላ ካርድ ይሰጣል ወይም አቤቱታው የቀረበው በምርጫው ቀን ሲሆን ድምጽ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ በመራጮች መዝገብ ላይ ቀድሞ የተሰጠ ካርድ ቀሪ ኮፒ ላይ ውድቅ የተደረገ ተብሎ ምልክት ይደረግበታል፡፡ የተበላሸውን ካርድ ይዞ ከቀረበ እንዲመልስ ይደረጋል።

