Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የለውጡ ዓመታት የፊስካል ፖሊሲ እና የፋይናንስ እርምጃዎች ስኬቶች …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ሀገራዊ ለውጡ እውን መሆኑን ተከትሎ በፊስካል ፖሊሲ እና ፋይናንስ በተደረጉ ማሻሻያዎች በርካታ ስኬት ተመዝግቧል አለ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ እንዳመለከተው፤ የመንግሥት የበጀት ጉድለት፣ የገቢ ዕድገት፣ አነስተኛ ገቢ ያለውን ህብረተሰብ ለመደገፍ የሚመደብ በጀት፣ የበጀት አስተማማኝነት እንዲሁም የዋጋ መረጋጋት እና የፋይናንስ አስተዳደርን ማዘመን ላይ የተሰሩ ስራዎች ውጤት አምጥተዋል።

የመንግሥት የበጀት ጉድለትን ለመቀነስ በተወሰደው ርምጃ ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት -2 ነጥብ 5 በመቶ የነበረውን የበጀት ጉድለት ወደ -0 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል።

የመንግሥት ገቢን ለማሻሻል በተተገበሩ የታለሙ ማሻሻያዎች አጠቃላይ ገቢው ከአምስት እጥፍ በላይ ማደጉን መረጃው ጠቁሟል።

የመንግሥትን ወጪ ለድህነት ቅነሳ ተግባራት ለማዋል በተሰራው ስራ አነስተኛ ገቢ ያለውን ህብረተሰብ ለመደገፍ የሚውለው የመንግሥት ወጪ ከአምስት እጥፍ በላይ ጨምሯል ብሏል።

የመካከለኛ ጊዜ የፊስካል ማዕቀፍ የበጀት ተዓማኒነትን ለማረጋገጥ ያስቻለ ሲሆን፤ ይህም የተሻሻለ የበጀት አፈጻጸምን ማምጣቱን አረጋግጧል።

የዋጋ ንረትን ለመቀልበስ በተደረገው ጥረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይወሰድ የነበረው ቀጥተኛ ብድር እንዲቋረጥ መደረጉን ያስታወሰው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ በዚህም ውጤት ማምጣት መቻሉን አመልክቷል።

መንግሥት የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ስርዓት መዘርጋቱን ገልጾ፤ የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን በመተግበር የፋይናንስ ስርዓቶችን በማዘመን የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ማዘመን እንደተቻለ ገልጿል።

Exit mobile version