Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ስጋት የደቀነው የሃዋይ ኪላዌ እሳተ ገሞራ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን ፓስፊክ ውቅያኖስ የሚገኘው የሃዋይ ኪላዌ እሳተ ገሞራ ተከታታይ ፍንዳታዎችን መፍጠሩን ተከትሎ በአካባቢው ስጋት መደቀኑ ተሰምቷል፡፡

በዓለም ከሚገኙ ከባድ እሳተ ገሞራዎች አንዱ የሆነው የሃዋይ ኪላዌ እሳተ ገሞራ በትናንትናው ዕለት በፈጠረው ፍንዳታ እስከ 400 ሜትር ድረስ ከፍታ ያላቸውን የእሳተ ገሞራ ፍንጣቂዎችን ወደ አየር መወርወሩ ተገልጿል፡፡

በፍንዳታው ከፍተኛ የአመድ እና ቅልጥ አለቶች (ላቫ) መሬት ላይ መውደቃቸውን ተከትሎም በአካባው የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮች እና ዋና ዋና መንገዶች በጊዜያዊነት ተዘግተዋል፡፡

የሃዋይ ኪላዌ እሳተ ገሞራ ለዓመታት በተለያዩ ጊዜያት በሚያስከትለው ፍንዳታ የአካባቢውን ማህበረሰብ እና የቱሪስቶችን ትኩረት ይስብ እንደነበር ተገልጿል።

ከፈረንጆቹ 2024 ወዲህ ትናንት 43ኛ ፍንዳታ ያስከተለው የሃዋይ ኪላዌ እሳተ ገሞራ፤ ከሰሞኑ የተከሰተው ፍንዳታ ስጋት መፍጠሩ ተነግሯል።

ፍንዳታው ከፍተኛ መጠን ያለው አመድ፣ ጭስ እና እሳት አዘል ቅልጥ አለት አስከትሏል ሲል ሲቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version