Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ አበባ የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር አምስት መዳረሻዎች መካከል አንዷ ሆነች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር አምስት መዳረሻዎች መካከል አንዷ ሆነች።

በበርካታ የዓለም ከተሞች መዳረሻውን የሚያደርገው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ውድድር በአዲስ አበባ ሲደረግ በዓለም አትሌቲክስ የነሐስ ደረጃ እንደተሰጠው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር የማዘጋጀት እድል ማግኘቷን የገለጸው ፌዴሬሽኑ÷ የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪ የዓለም አትሌቲክስ የነሐስ ደረጃ የተሰጠው ሲሆን የፊታችን ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይደረጋል ብሏል።

የዓለም አትሌቲክስ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት አዳዲስ የኮንቲኔንታል ቱር ውድድሮች ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ሌሴቶ፣ ኦማን እና ሳዑዲ አረቢያ ይገኙበታል።

Exit mobile version