Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢራቅ በሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራቅ በጀልባ ላይ በተጠመደ ቦምብ በሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የወደብ ኩባንያዎች አስታውቀዋል፡፡

በሀገሪቱ ባስራ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ ሌሊት በተፈጸመው ጥቃት መርከቦቹ በእሳት የተያያዙ ሲሆን፥ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የኢራቅ ወደቦችን የሚያስተዳድረው ኩባንያ ገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎ በመርከቦቹ ላይ የነበሩ 25 ሰዎችን ህይወት ማትረፍ መቻሉንና ሌሎች ሰዎችን ለመታደግ ፍለጋዎች መቀጠላቸውን የኩባንያውን ኃላፊ ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ጥቃቱ የኢራን እንደሆኑ በታመነባቸው ሁለት ጀልባዎች ላይ በተጠመደ ቦምብ መፈጸሙ የተገለጸ ሲሆን፥ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የኢራቅ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ማቆማቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በሁለቱ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ጨምሮ በቀጣናው ከሰሞኑ መጠነ ሰፊ ግጭት ከተጀመረ ወዲህ 16 መርከቦች የጥቃት ሰለባ መሆናቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

Exit mobile version