Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦችን አፅናኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ ተገኝተው በመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች ቤተሰቦችን አፅናንተዋል።

አደጋው በደረሰበት አካባቢ አስክሬን የማፈለለጉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡

በደረሰው አደጋ የሰው ሕይወት ከማለፉና ንብረት ከመውደሙ ባሻገር 3 ሺህ 480 አባላት ያሏቸው 575 ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል።

ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖችን አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን በዘላቂነት ለማቋቋም ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

በአርባ ምንጭ ከተማና በጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የኩልፎ ወንዝ ሙላት ያስከተለውን ጉዳት በትናንትናው ዕለት ተዘዋውረው የተመለከቱት አፈ ጉባዔው፤ ዜጎች በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

Exit mobile version