Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሦስት ቀናት ሀዘን ታወጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት ናዳ እና የጎርፍ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች በክልሉ የሦስት ቀናት ሀዘን ታውጇል፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ኃይለማርያም ተስፋዬ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፥ በአደጋው ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች በክልሉ የታወጀው ሀዘን ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነው፡፡

በአደጋው የበርካታ ዜጎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ምግብና የጤና አገልግሎትን ጨምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version