አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ9 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።
ከየካቲት 28 ቀን ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በዲጅታል እና በማኑዋል አማራጭ እየተከናወነ ይገኛል።
የመራጮች ምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳሉት፤ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ እስካሁን ድረስ 9 ሚሊየን 36 ሺህ 994 መራጮች ተመዝግበዋል።
ከ46 ሺህ በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባም እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዙፋን ካሳሁን

