Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ‘ፍቼ ጫምባላላ’ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ‘ፍቼ ጫምባላላ’ በዛሬው ዕለት በልዩ ልዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት መከበር ጀምሯል፡፡

ፍቼ ጫምባላላ ለሀገራዊ መግባባት፣ ለአንድነትና ለሰላም ጉልህ አበርክቶ ያላቸውን እሴቶች አቅፎ የያዘ በዓል ነው፡፡

የበዓሉ የእርቅ፣ የሰላምና የአንድነት እሴቶች ከ11 ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይደሳስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ አስችለውታል፡፡

ፍቼ ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ አሮጌውን ዓመት ሸኝቶ አዲሱን የሚቀበልበት ብቻ ሳይሆን የተጣሉ የሚታረቁበት፣ ትውልድ ከሽማግሌዎች ምርቃትና እውቀት የሚቀስምበት እንዲሁም ማህበረሰባዊ ትስስር የሚጸናበት ውብ የባህል አውድ ነው።

የበዓሉ ዋዜማ የሆነው “ፊጣሪ ሃዋሮ” በዛሬው ዕለት በደማቅ ስነ ስርዓቶች መከበር ጀምሯል፡፡

Exit mobile version