Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያስተማራቸውን 792 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 792 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት በመጠቀም በሀገሪቱ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ተመራቂዎች የሀገርን ምርታማነትን ማሳደግ፣ የጤና አገልግሎትን ማሻሻልና ህብረተሰቡ የሚያገኘውን የፍትህ አገልግሎት ለማጠናከር በትጋት መስራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው፥ በጤና ዘርፍ የተመረቁ ተማሪዎች ህብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ በመሥራት ለሀገር እድገትና ብልጽግና አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።
በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ መሰረት ኃይሉን ጨምሮ ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
በገላና ተስፋዬ
Exit mobile version