Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማረጋገጥ እየተፋለሙ የሚገኙና ተመሳሳይ ነጥብ ይዘው በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ እና 4ኛ ላይ የተቀመጡት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አዲስ አሰልጣኝ ከቀጠሩ በኋላ ጠንካራ አቋም እያሳዩ የሚገኙት ቀያዮቹ ሰይጣኖች በሜዳቸው ኦልድ ትራፎርድ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ አስቶን ቪላን ያስተናግዳሉ።

እንዲሁም ምሽት 1፡30 ሰዓት ላይ ሊቨርፑልን ከቶተንሃም ሆትስፐር የሚያገናኘው ሌላኛው የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ ይደረጋል።

የመውረድ አደጋ የተደቀነበት የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ወደ አንፊልድ ተጉዞ የአምናውን የሊጉ ሻምፒዮን ሊቨርፑልን ይገጥማል።

የእለቱ የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ክሪስታል ፓላስ ከሊድስ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከፉልሃም ጨዋታቸውን በተመሳሳይ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ።

በዮናስ ጌትነት

Exit mobile version