Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጋዜጠኛ ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀድሞ ፋና ሬዲዮ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጠኛ የነበረው ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በ1957 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ ወረዳ የተወለደው ጋዜጠኛ ታሪኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።

ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ ቀድሞ ፋና የአሁኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሸን በመቀላቀል በአፋን ኦሮሞ ክፍል በሚዲያው ዘርፍ የኦሮሞን ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ በማሳደግ ረገድ የበኩሉን ሚና ተጫውቷል።

ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት የነበረው ጋዜጠኛ ታሪኩ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሌሊት በተወለደ በ61 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የጋዜጠኛ ታሪኩ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በሚገኘው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለቤተሰቦቹና ዘመድ ወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል።

በምናለ ገበየሁ

Exit mobile version