Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

“እንዛታ” የተሰኘ ትውፊታዊ ቴአትር ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዝማሪዎች ሕይወት እና ሥራዎች ላይ የተመሰርቶ “እንዛታ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ትውፊታዊ ቴአትር በዛሬው ዕለት በባሕርዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ ተመርቋል።

ቴአትሩ “ቡርቧክስ” በተባለችው የአዝማሪዎች መንደር ውስጥ በተደረገ ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የቴአትሩ ደራሲ ንብረት ያለው እንዳሉት÷ አዝማሪዎች ወይም ዓለም አጫዋቾች ለሀገር ግንባታና እድገት የተለያየ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

በመሆኑም የአዝማሪዎችን ውለታ አስጠብቆ እና ሙያውን አሳድጎ  መቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አዝማሪ በሙዚቃ የሚያጫውት ብቻ ሳይሆን ዘገባ ነጋሪና ደስታን አብሳሪ፣ የህዝብ ፍላጎትና ስሜት አንጻባራቂ፣ ችግር ጠቋሚ እና መፍትሄ አመላካች በመሆን እንደየ አውዱ ይከሰታል ብለዋል።

የአማራ ክልል ባህል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ገብረማርያም ይርጋም በበኩላቸው÷  የክልሉን ታሪክ እና ቅርስ በኪነጥበብ ለማስተዋወቅ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ቴአትርም የዚህ አካል እንደሆነ ጠቅሰው፤ ይህንን ዓይነት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በታምሩ ከፈለኝ

Exit mobile version